October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሂዝቦላህ አደረጃጀት ተለዋዋጭ መሆን ለእስራኤል ፈተና ሊሆንባት እንደሚችል ተገለጸ

ቡድኑ ከውጊያ ግንባሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ሰንዝሯልየሂዝቦላህ አደረጃጀት ተለዋዋጭ መሆን ለእስራኤል ፈተና ሊሆንባት እንደሚችል ተገለጸ፡፡ከ11 ወራት በፊት የፍልስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነበር በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የተቀሰቀሰው፡፡እስራኤል ሐማስ በሚንቀሳቀስበት ጋዛ ውስጥ ባደረሰችው ጥቃት ከ41 ሺህ በላይ ንጹሃን የተገደሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ይህ ጦርነት ወደ ሊባኖስ ዞሯል፡፡የሊባኖሱ ሂዝቦላህ ወታደራዊ ቡድን ከፍልስጠየማዊን ጎን እንደሚቆም ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ በእስራኤል ላይ ጥቃት ሲሰነዝር የቆየ ሲሆን አሁን ላይ ጦርነቱ ከጋዛ ወደ ሊባኖስ ዞሯል፡፡ከሁለት ሳምንት በፊት በኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በቤሩት በርካቶች ሲሞቱ ከ2 ሺህ በላይ ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ የተተኮሱ 105 ሮኬቶችን መትቼ ጥያለሁ አለእስራኤል የሂዝቦላህ አመራሮችን፣ ተዋጊዎችን እና የውጊያ መጋዝኖችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ሰንዝራለች፡፡ይህን ተከትሎ የእስራኤል ሂዝቦላህ ጦርነት የተባባሰ ሲሆን በዛሬው ዕለት ብቻ ከውጊያ ግንባር 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የባሊስቲክ ሚሳኤል በሂዝቦላህ ተፈጽሟል፡፡የእስራኤል የስለላ ተቋም ሞሳድን ኢላማ ለማድረግ የተተኮሰው ሚሳኤል መክሸፉን የሀገሪቱ አየር ሀይል አስታውቋል፡፡ሮይተርስ የመካከለኛው ምስራቅ ተንታኞችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ እስራኤል ከሂዝቦላህ ጋር የጀመረችው ጦርነት ለረጅም ጊዜ በላይ ሊቆይ እንደሚችል ተገልጿል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ሂዝቦላህ ከሐማስ ተዋጊዎች የሚለይባቸው በርካታ ጥንካሬዎች አሉት የተባለ ሲሆን ለአብነትም ረጅም ርቀት እና ጥንካሬ ያላቸው የመሬት ውስጥ ምሽጎች መያዙ፣ 100 ሺህ ተዋጊዎች እና ተተኳሾች መያዙ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ቡድኑ አሁን ለይ ከ150 ሺህ በላይ ሮኬቶችን ታጥቋል የተባለ ሲሆን ሰሜን ኮሪያ፣ ኢራን እና ቻይና ሰራሽ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉተም ተገልጿል፡፡እንዲሁም የሂዝቦላህን አደረጃጀት እስራኤል በቀላሉ የቡድኑን ወታደራዊ አዛዦች በመግደል ብቻ ልታፈርሰው እንደማትችልም ተንታኞቹ ተናግረዋል፡፡ሂዝቦላህ ከሰሞኑ በእስራኤል ጥቃት በተገደሉ ወታደራዊ አመራሮቹ ምትክ ወዲያውኑ አዲስ የጦር አዛዦችን መምረጡንየሂዝቦላህ ተዋጊዎች ከከተማ ርቀው በእስራኤል ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ መሆናቸው፣ ተተኳሶች በመሬት ውስጥ በተቆፈሩ አለታማ ምሽጎት ውስጥ መሆናቸው እስራኤል በቀላሉ በአየር ጥቃት ብቻ ለማውደም ሊከብዳት ይችላልም ተብሏል፡፡ይህን ተከትሎም የእስራኤል-ሂዝቦላህ ጦርነት በትንሽ ጊዜ ሊቆም የማይችል እና ጉዳቱም ከፍተኛ ሊሆን ይችላልም ተብሎ ተሰግቷል፡፡

Al-Ain