October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

እንግሊዝ በፀጥታው ዘርፍ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ገለፀች

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልችን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ኮሚሽነር ጀነራሉ በውይይቱ ወቅት ከእንግሊዝ የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ (UK National Crime Agency) ጋር እየተጠናከረ ስለመጣው ትብብር አንስተዋል።ሁለቱ ወገኖች በተለይ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ በጋራ ለመስራት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥር የተቋቋመውን የሬድ ፎክስ ማዕከል (Red Fox Center) በማቴሪያልና በስልጠና ስለማጠናከር መክረዋል።ኮሚሽነር ጀነራሉ ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በእንግሊዝ ሀገር እየተሰጠ ላለው የፊኖባንክስ የትምህርት ዕድል (Finobanks Scholarship) ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ተወያዮቹ በቀጣይ መሰል እድሎቹን ስለማስፋት እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እየተገነባ ያለውን የፎረንሲክ ማዕከል በማቴሪያል፣ በአቅም ግንባታ እና በልምድ ልውውጥ ስለመደገፍ መክረዋል። አምባሳደር ዳረን ዋልች ሀገራቸው በፀጥታው ዘርፍ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።በቀጣይ ትብብሩን የተሻለ ደረጃ ለማድረስ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በእንግሊዙ ብሔራዊ የወንጀል ኤጀንሲ መካከል የሚፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

EBC