January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የ2017 ዓ ም ለሚከበረው የሸካቾ ዘመን መለዋጫ በዓል (ማሽቃሮ) እንኳን በሠላማዊ መንገድ እንድከብር ትኩረት ሰጥተው እየሰራ መሆኑን የአንድራቻ ወረዳ ሠላም ጸጥታና ሚላሽ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የአንድራቻ ወረዳ ሠላም ጸጥታና ሚላሽ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳ ገሊቶ እንደገለጹት ተቋሙ ሁሌም የህዝቡን ሠላም ደህንነትና አንድነት በመጠበቅ የህዝብ ለህዝብ ግንኑኝነትን ሰላማዊ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ስራ እንድገባ ማድረግ ነው ብለዋል።በመስከረም 20/2017 ዓ ም በጌጫ ከተማ ለሚከበረው የሸካቾ ዘመን መለወጫ በዓል(ማሽቃሮ) በሠላም እንድከበር ከሚመለከተው አካላት ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ጸጥታ አካላትን በማደራጀት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ጽህፈት ቤቱ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ካሳሁን ደንበሎ