January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በፓኪስታን የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

ኢትዮጵያ በፓኪስታን ካይበር ፓክቱንክዋ በተባለው ግዛት የደረሰውን የሽብር ጥቃት አውግዛለች። ጥቃቱ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታ ዲፕሎማቶችን የያዘ ተሽከርካሪ ላይ መፈጸሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ዲፕሎማቶቹን ሲያጅብ በነበረው የፖሊስ ኦፊሰር ህልፈት ለቤተሰቦች፣ ለፓኪስታን ሕዝብና መንግስት መጽናናትን እንደምትመኝም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

EBC