January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የካፌቾ ብሔረሰብ የቋንቋ እና የባህል ሲምፖዚየም በቦንጋ ከተማ እየተካሔደ ነው

የካፌቾ ብሔረሰብ የቋንቋ እና የባህል ሲምፖዚየም በቦንጋ ከተማ እየተካሔደ ይገኛል፡፡ ሲምፖዚየሙ የብሔረሰቡን የዘመን መለወጫ በዓል ማሽቃሮ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።የማሽቃሮ በዓል በቦንጋ ከተማ በነገው ዕለት ይከበራል።ማሽቃሮ የዘመን መለወጫ በዓል የክረምቱ ወቅት አልፎ ብርሃናማው ጊዜ መግባቱ የሚበሰርበት ነው።የእርቅ፣ የሰላም እና የአንድነት መገለጫ በሆነው ማሽቃሮ ቀጣዩ ጊዜ የፍቅር እና የልማት እንዲሆን ሁሉም የብሔረሰቡ አባት ምርቃት የሚያገኙበት እንደሆነም የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል።

EBC