የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በ2023 31.4 ቢሊየን ዶላር ደርሷልየ50 አመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አረብ ኤምሬትስ እና አሜሪካ በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን እያጠናከሩ ነው።የኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በዋይትሃውስ ከአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።ኢኮኖሚና ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የታዳሽ ሃይል ልማት፣ የህዋ ምርምርና ቴክኖሎጂ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ይሆናሉ ተብሏል።ኤምሬትስ ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ክልል የአሜሪካ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ ሀገር ናት።
EBC
More Stories
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ከትራምፕ መመረጥ በኋላ የጎልፍ ጨዋታ ልምምድ ጀመሩ
ዶናልድ ትራምፕ ተጨማሪ ሹመቶችን ለማን እንደሚሰጡ ፍንጭ ሰጡ
በ2025 ምርጫ የሚያደርጉ ሀገራት እነማን ናቸው?