ኪንግ አንድ አመት እስር ቢፈረድበትም ቅጣቱ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ስለተሰላለት ከእስር መለቀቁን ጠበቃው ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ዘገባው ጠቅሷልወደ ሰሜን ኮሪያ ኮብልሎ የነበረው የአሜሪካ ወታደር ከእስር ተለቀቀ።ባለፈው አመት ወደ ሰሜን ኮሪያ ከገባ በኋላ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የአሜሪካ ወታደር ትራቪስ ኪንግ በትናንትናው እለት የአንድ አመት እስር ከተላለፈበት በኋላ መለቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል።ኪንግ አንድ አመት እስር ቢፈረድበትም ቅጣቱ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ስለተሰላለት ከእስር መለቀቁን ጠበቃው ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ዘገባው ጠቅሷል።በቴክሳስ ፎርት ብሊስ በተካሄደ የፍርድ ሂደት ኪንግ በአምስቱ ክሶች ጥፋተኛ መሆኑን አምኗል።የአሜሪካ ጦር ኪንግን በ2023 ወደ ሰሜን ኮሪያ በመኮብለል፣ ሌሎች ወታደሮችን በማጥቃት፣ ህጻናትን ለወሲብ ቪዲዮዎች በመመልመል ጨምሮ በሌሎች ወንጀሎች ባለፈው አመት ክስ መስርቶበት ነበር።ኪንግ በሚስጥር በተደረገ ደርድር በመስከረም 2023 ከሰሜን ኮሪያ እስር ከተለቀቀ በኋላ ጦሩ በወታደራዊ ህግ መሰረት በ14 ጥፋቶች ነበር የከሰሰው። ኪንግ በአምስቱ ክሶች ጥፋተኝነቱን ስላመነ መንግስት ዘጠኙን ክሶች አንስቶለታል።”ትራቪስ የተፈረደበትን ጊዜ ያህል በማሳለፉ እና ጥሩ ባህሪ በማሳየቱ፣ አሁን ከእስር ተለቆ ወደ ቤቱ ተመልሷል”ብሏል ጠበቃው።ኪንግ ወደ አሜሪካ ጦር የተቀላቀለው በፈረንጆቹ ጥር 2021 ነበር። ኪንግ በደቡብ ኮሪያ በነበረበት ወቅት ጥቃት በመፈጸም ታሰሮ ነበር። ኪንግ ከሰሜን ኮሪያ እስር ከተለቀቀ በኋላ አሜሪካ ውስጥ የስነስርአት ቅጣት ይጠብቀው ነበር።ኪንግ ወደ ቤቱ እየሄደ ባለበት ወቅት ነበር ከሴኡል አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመውጣት ወደ ሰሜን ኮሪያ ድንበር ያቀናው።ኪንግ ወደ ሰሜን ኮሪያ ግዛት ከገባ በኋላ ወዲያውኑ በሰሜን ኮሪያ ተይዞ ታስሮ ነበር።
Al-Ain
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች