የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት እስራኤል በሄዝቦላ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ትቀጥላለች ብለዋልየእስራኤል ጦር 100 የሄዝቦላ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን ገለጸ።የእስራኤል የጦር ጄቶች በትናንትናው እለት በደቡብ ሊባኖስ ባደሱት ድብደባ ወደ እስራኤል ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ የሚውሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሮኬት ማስወንጨፊያ ባረሎችን ማውደማቸውን ጦሩ አስታውቋል።ጦሩ እንደገለጸው የጦር ጄቶቹ 1000 ባረሎችን የያዙ 100 ማስወንጨፊያዎች መትተዋል።”የእስራኤል ጦር የእስራኤልን ህልውና ለማስጠበቅ የሽብርተኛውን ሄዝቦላ መሰረተልማቶች የመሸርሸር እና አቅሙን የማዳከም ዘመቻ ይቀጥላል” ብሏል ጦሩ። ይህ ከባድ ጥቃት ሊባኖስ እና ሄዘቦላ እስራኤልን ተጠያቂ ባደረጉት ጥቃት የሄዝቦላ የሬዲዮ መገናኛዎች እና “ፔጀርስ” ፈንድተው 37 ሰዎች ከተገደሉ እና 3000 ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ የተፈጸመ ነው።በሮይተርስ የሊባኖስ የደህንነት ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው ትናንት ከሰአት በኋላ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖንስ በደርዘን በሚቆጠሩ ቦምቦች ጥቃት ፈጽማለች። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት እስራኤል በሄዝቦላ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ትቀጥላለች ብለዋል።የእንግሊዝ ፎሬን ሴክሬታሪ ዴቪድ ላሚ ከአንድ ሳምንት ውጥረት በኋላ በእስራኤል እና በሊባኖሱ ሄዝቦላ መካከል ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።አሜሪካም ውጥረቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባታል።ባለፈው ረቡዕ እለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር አቅራቢያ የተፈናቀሉ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን እንደሚመልሱ ዝተዋል።በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገረው የሊባኖሱ ሄዘቦላ ወደ እስራኤል መተኮስ የጀመረው የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለፍልስጤሙ ሀማስ አጋርነት ለማሳየት ነበር። በጥቃቱ በድንበር አካባቢ ይኖሩ የነበሩ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ወደ መሀል ለመፈናቀል ተገድደዋል። ከጦርነቱ መቀስቀስ ወዲህ እስራኤል እና ሄዝቦላ በየቀኑ በሚባል ደረጃ የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ
Al-Ain
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች