ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረቶችን ሰርቀዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ተኩል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ 5 በመገንባት ላይ በሚገኘው አዳምስ ህንፃ ላይ የተዘረጉ የኤሌትሪክ ገመዶችን ለመስረቅ ሁለት ተጠርጣሪዎች አጥር ዘለው ሲገቡ በወቅቱ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ተይዘው ሲፈተሹ የኬብል መቁረጫና ሁለት ቦርሳ እንደተገኘባቸው ፖሊስ ጠቅሷል። የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ ማስፋት ስራ መስራቱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። በምርመራ ማስፋት ሥራው ግለሰቦቹ በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 በፀጋ ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኘው አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የሰረቁትን ንብረት እንደሚያስረክቡ በመረጋገጡ በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ 50 ጥቅል የኤሌትሪክ ገመዶች፣ 5 ጥቅል የኤል ኢ ዲ ኬብል፣ ልዩ ልዩ አይነት ሌሎች ኬብሎች እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከአዳምስ ህንፃ የተሰረቁ የኤሌትሪክ ገመዶች መገኘቱን ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል። ከዚህ የወንጀል ድርጊት ጋር በተገናኘ የስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩና የተሰረቀ እቃ የሚገዙ ሁለት ተቀባዮች ተይዘው ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።