January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት መለኪያ ደረጃዋን አሻሻለች

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት መለኪያ ደረጃዋን አሻሻለች፡፡በየሁለት ዓመቱ የሚወጣው የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፋዊ የኢ-መንግሥት መለኪያ ትናንት በኒዮርክ ከመንግሥታቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ይፋ ሆኗል።ይህ ዓለም አቀፋዊ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት መለኪያ የዓለም ሀገራት በየሁለት ዓመቱ ከሌሎች ሀገራት አንጻር እና በራሳቸው ካሳዩት እድገት ጋር በማነጻጸር ሀገራቱ በዘርፉ ያደረጉትን መሻሻሎች ብሎም ያስመዘገቧቸውን ለውጦች የሚያሳይ ነው።በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት ሪፖርት መሠረት ኢትዮጵያ ከነበረችበት 10 ደረጃዎችን ማሻሻል ችላለች፡፡

FBC