January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢጋድ ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን የፊታችን መስከረም 9 ይፋ ይሆናል

የቱሪዝም መረጃ የሚያዝበት”የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት” ዝግጅት ተጠናቅቆ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ በሰጡት መግለጫ ÷ኢጋድ እና አባል ሀገራቱ ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን በቀጣናው እውን ለማድረግ ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን ሲያዘጋጁ መቆየታቸውን ገልጸዋል ።በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሚተገበረው ማስተር ፕላኑ የቀጣናው ሀገራት የተቀናጁና ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል፡፡ማስተር ፕላኑ የፊታችን መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይፋ የሚደረግ ሲሆን÷ከዚህ ጎን ለጎንም ከመስከረም 7 እስከ 9 ቀን የኢጋድ ቱሪዝም ዓውደ ርዕይ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።ኢትዮጵያ ይህንን ዓውደ ርዕይ ማዘጋጀቷ ሀገራት በአዲስ አበባ የቱሪዝም ሃብታቸውን እንዲያስተዋውቁና የንግድ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።በዕለቱ የቱሪዝም መረጃ የሚያዝበት “የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት” ዝግጅት ተጠናቅቆ ይፋ የተደረገ ሲሆን÷ አካውንቱን አዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ከ6 ወር ያህል ጊዜ መውሰዱ ተመላክቷል፡፡የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት በዘርፉ ያሉ አጠቃላይ መረጃዎችን በአግባቡ ለመሰነድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡

FBC