January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አባ ፍራንሲስ አሜሪካዊያን “የተሻለውን ሰይጣን” እንዲመርጡ ጥሪ አቀረቡ

ስም ያልጠቀሱት አባ ፍራንሲስ 50 ሚሊዮን የካቶሊክ ዕምነት ተከታይ አሜሪካኖች በምርጫ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋልአባ ፍራንሲስ አሜሪካዊያን “የተሻለውን ሰይጣን” እንዲመርጡ ጥሪ አቀረቡ፡፡የሮማን ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያንሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በደቡባዊ እስያ የ12 ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡በጉብኝታቸው ማጠቃለያ ላይ መግለጫ የሰጡት አባ ፍራንሲስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች ሰይጣኖች መሆናቸውን የሚያሳይ ንግግር አድርገዋል፡፡አሜሪካ ጽንስ ማቋረጥ አልያም ውርጃን የምትፈቅድ እና ስደተኞችን የሚጠላ እጩ ፕሬዝዳንቶች አሉ ያሉት አባ ፍራንሲስ አሜሪካዊያን የካቶሊክ አማኞች ከሁለቱ አንዱን ሰይጣን የመምረጥ ምርጫ ውስጥ ገብተዋል ብለዋል፡፡እንደ አባ ፍራንሲስ ገለጻ ከአሜሪካ ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ 50 ሚሊዮን ያህሉ የካቶሊክ ዕምነት ተከታይ ናቸው፡፡ፖፕ ፍራንሲስ አሁኑኑ እንዲሞቱ የጸለዩ ቄሶች ይቅርታ ጠየቁአሜሪካዊያን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በምርጫው እንዲሳተፉ እና ድምጻቸውን የባሰ ሰይጣን ላልሆነው እጩ እንዲሰጡም አባ ፍራንሲስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡አባ ፍራንሲስ ስም ባይጠቅሱም ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች ላይ ከረር ያለ አቋም በመያዝ የሚታወቁ ሲሆን ምርጫውን አሸንፈው ስልጣን ከያዙ ስደተኞችን ከሀገራቸው እንደሚያባርሩ በተደጋጋሚ ቃል ገብተዋል፡፡እንዲሁም ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ካማላ ሀሪስ ጽንስ ማቋረጥ መብት መሆኑን በምርጫው ስልጣን ከያዙ ይህንን እንደሚያስፈጽሙ ተናግረዋል፡፡አባ ፍራንሲስ ሁለቱም ስራዎች የሰይጣን ስራዎች ናቸው ያሉ ሲሆን ስደተኛ ስለመጣ የተለየ ችግር አይደርስም፣ ጽንስን ከማህጸን ውስጥ ማውጣት ከነፍስ ግድያ አይተናነስም ሲሉ ኮንነዋል፡፡

Al-Ain