October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጥረት በጋራ ልማት ቀጣናዊ ትስስር መፍጠርና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው – አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ

የኢትዮጵያ የሁልጊዜ ጥረት በጋራ ልማት ቀጣናዊ ትስስር መፍጠርና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ።አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የልማትና የንግድ ግንኙነቷን በማጠናከር ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማምጣት እየሰራች ትገኛለች።በዲፕሎማሲው መስክም መልካም ግንኙነቶችን በማጠናከርና የሚደርሱ ጫናዎችን ጭምር በመቋቋም ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እያስመዘገበች ነው ብለዋል።የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጥቅሞች የዛሬን መሻትና የወደፊት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረጉ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጥረት በጋራ ልማት ቀጣናዊ ትስስር መፍጠርና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ፣ በሰጥቶ መቀበል መርህ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑንም አረጋግጠዋል።የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ እንዳይሳለጥ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም የመንግሥት ጥረት የቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና እድገት ዋነኛው መሰረት ሰላም መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ታዬ፤ ለዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ሁለንተናዊ እድገት መረጋገጥ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

EBC