January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የጤና ሚኒስቴር እና ብሔራዊ መታወቂያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን ጎብኝተዋል። ሚኒስትሯ እና ኃላፊዎቹ ከፕሮግራሙ አመራሮች ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከጤና ዘርፍ ጋር ስለሚኖረው ትሥሥር ተወያይተዋል። በቀጣይ ብሔራዊ መታወቂያ ለጤናው ዘርፍ በሚጠቅምበት ጉዳይ ላይ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል።የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ እና የሥራ ኃላፊዎቹ ለፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ማድረጋቸውንም ከብሔራዊ መታወቂ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።