January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አርጀንቲና በኮሎምቢያ መሸነፏን ተከትሎ ግብ ጠባቂው ማርቲኔዝ ያሳየው ድርጊት አነጋገረ

ኮሎምቢያ የአርጀንቲናን ለ12 ጨዎታዎች ያለመሸነፍ ሩጫን ገትታዋለችበ2026ቱ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አርጀንቲና በኮሎምቢያ መሸነፏን ተከትሎ የአርጀንቲና ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ ያሳየው ተግባር አነጋጋሪ ሆኗል።በትናንትናው እለት በባራንቁይላ በተካሄደው የማጣሪያ ጨዋታ የኳታሩን የአለም ዋንጫ ያሸነፈችው አርጀንቲና በኮሎምቢያ 2-1 በሆነ ውጤት መሸነፏ ያናደደው ማርቲኔዝ ካሜራ በጥፊ ሲመታ ታይቷል።ኮሎምቢያ የአርጀንቲናን ለ12 ጨዎታዎች ያለመሸነፍ ሩጫን ገትታዋለች።በጉዳት ምክንያት አምበሉን ሊዮነል ሜሲን ያላሰለፈው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ኢላማውን የጠበቀ አንድ ሙከራ ብቻ ነው ያደረገው።በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ የርሰን ማስኮየራ ለኮሎምቢያ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ኒኮላስ ጎንዛሌዝ ደግሞ በ48ኛው ለአርጀንቲና የአቻነቷን ግብ ማስቆጠር ችሎ ነበር። ነገርግን ጄምስ ሮድሪጊዝ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግብ በማስቆጠሩ ኮሎምቢያ በማጣሪያ ጨዋታው ሁሉንም ሶስት ነጥቦች መሰብሰብ ችላለች።የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በእስካሁኑ የማጣሪያ ጨዋታ ተሸንፎ ስላማያውቅ፣ መሸነፋቸውን ለመቀበል ይቸገራሉ። የአስቶን ቪላ ግብ ጠባቂ የሆነው ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ ሙሉ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ሲከታተለው የነበረውን ካሜራ በጥፊ ለመምታት ሲቃጣ ታይቷል።ማርቲኔዝ በሜዳ ላይ አነጋጋሪ ተግባር ሲፈጽም ይህ የመጀመሪያው አይደለም።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአለምዋንጫ አሸናፊውን ቡድን ባጅ ቲሸርቱ ላይ ያጻፈው የቶትንሃሙ ተከላካይ ተጨዋች ክርስቲያን ሮሜሮ የኮሎምቢያ ደጋፊዎች በአርጀንቲና የቡድን ጓዶቹ እና በራሱ ላይ ያሳዩትን ያልተገባ ድርጊት ተቃውሟል።የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አስልጣኝ ሊዮነል ስካሎኒ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት መግለጫ ብዙ ጉዳዮችን አንስተዋል።ስካሎኒ ለኮሎምቢያ ቡድን የደስታ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ስካሎኒ እንደገለጹት ኒኮላስ ኦተመንዲ በዳንኤል ሙኖዝ ላይ ያደረገውን መንሸራተት በቫር ከታየ በኋላ ዳኛው የሰጡት ፍጹም ቅጣት ምት አሳዝኗቸዋል።የአርጀንቲናው አስልጣኝ አክለውም ኮሎምቢያ ጨዋታውን 2-1 መሞራት ከጀመረች በኋላ በተደጋጋሚ እና በተሳካ ሁኔታ ሰአት አባክናለች የሚል ቅሬታም አቅርበዋል።

al-ain