ድጋፉን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፋት የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድሙ ግርማ ይህ ዓይነቱ ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረዉ ይሰራል ብለዋል።በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችንና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር 350 ለሚሆኑ ለተቸገሩ ወገኖች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለእያንዳዳቸዉ የ 2 ሊትር ዘይትና የ4 ኪሎ ግራም ዱቄት ድጋፍ መበርከቱን የተናገሩት ደግሞ በቴፒ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሴቶች ሊግ ሀላፊ ወይዘሮ ይጋርዱ ጤናዉ ናቸዉ። በተመሳሳይ በከተማዉ መዋቅር ዉስጥ የሚሰሩና ከ2 ሺህ ብር በታች የሚከፈላቸዉ 126 ደመወዝተኞችም ለእያንዳንዳቸዉ የ5 ሊትር ዘይት ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል። ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ።
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።