January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የማሻ ማረሚያ ተቋም ከ2 መቶ በላይ የህግ ታራሚዎችን ይቅርታ አድርጓል።

የማሻ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር ደነቀ እዳሮ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ- አዋጅ ቁጥር 30/2016 እንዲሁም የይቅርታ ቦርድ መመሪያ አፈጻጸም ቁጥር 1/2016 መሠረተል ከ268 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አገኝተዋል ብለዋል።

የሸካ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አድራሮ ይቅርታ ለተደረገላቸው ታራሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት ማረሚያ ተቋም ስራው ማረምና ማነጽ መሆኑን ገልጸው በማረሚያ ቆይታቸው ጥሩ ስነ _ ምግበር ያሳዩትን መንግስት በይቅርታ መፍታቱን በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።