October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

“በሀገራችን ጥቅም ለማንደራደር ኢትዮጵያውያን፤ ሉዓላዊነት የማንነታችን ዋና መሰረት ነው፡፡

ዛሬ የሀገራችን የሉዓላዊነት የክብር ከፍታ ሳይዛነፍ እንዲጠበቅ ላደረጉ ዜጎች ከፍ ያለ ክብር ለመስጠት በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና የፓናል ውይይት ተገኝተናል፡፡

ይህ ቀን የትናንት መስዋዕትነትን መዘከሪያ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላለችውና ነገ ፀንታ ለምትኖረው ኢትዮጵያም ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር ለሚተጉ ዜጎች ጭምር የተሰናዳ መዘክር ነው።

የዚህ ትውልድ አባል የሆን እኛ፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ሲሉ ዋጋ የከፈሉ ውድ ኢትዮጵያውያን ዕዳ አለብን፡፡

በመሆኑም ይህንን ዕዳ ዘመኑ በሚጠይቀው ልክ ለመክፈልና የተረከብነውን አደራ ለመወጣት ቁርጠኝነታችንን በተግባር ማሳየት ይገባናል፡፡“

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ