ዱሮቭ በ5.5 ሚሊዮን ዶላር በዋስ ወጥቶ በሳምንት ሁለት ጊዜ ለፖሊሲ ሪፖርት እንዲያደርግ ታዟልየቴሌግራም ኃላፊ ዱሮቭ በፈረንሳይ የቀረበበት ክስ “ድንገተኛ” እና “የተሳሳተ” ነው አለ።የቴሌግራም መተግበሪያ ባለቤት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፖቬል ዱሮቭ ህገወጥ ይዘቶችን በማተም ጠርጥረው ባለፈው ወር ላሰሩት እና ለከሰሱት የፈረንሳይ ባለስልጣናት መልስ ሰጥቷል።ዱሮቭ ከታሰረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌግራም ገጹ በሰጠው ረጅም ጽሁፍ ሌሎች ሰዎች ላሰራጩት ይዘት ተጠያቂ መደረጉ እንዳሳዘነው ገልጿል።”ከስማርት ስልክ በፊት የነበሩ ህጎችን ተጠቅሞ ሌሎች ሰዎች ለፈጸሙት ለወንጀል ዋና ስራ አስፈጻሚ ተጠያቂ ማድረግ የተሳሳተ አካሄድ ነው” ብሏል።ቴሌግራም “ማንም የፈልገውን ይዘት የሚያሰራጭበት መድረክ” ነው የሚለውን ክስ እንደማይቀበለው የገለጸው ዱሮቭ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ መጥሮ ይዘቶችን እና ቻናሎችን በየቀኑ እያወረድን ነው”ብሏል።ፓሪስ ያቀረበችውን የትብብር ጥያቄ ቴሌግራም አልተቀበለም የሚለውን ክስ ወድቅ ያደረገው ዱሮቭ የፈረንሳይ ባለስልጣናት የሽብር ስጋት ለመከላከል የሚያስችል ‘ሆትላይን’ እንዲያቋቁሙ በግሉ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ገልጿል።ዱሮቭ እንደገለጸው በአሁኑ ወቅት የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር በመላው አለም 950 ሚሊዮን በመድረሱ ወንጀሎች መተግበሪያውን ያለአግባብ እንዲጠቀሙ ቀላል ሆኖላቸዋል። “ለዚህ ነው ይህን ለማሻሻል የግል አላማዩ አድርጌ እቅድ የያዝኩት።”የ39 አመቱ ዱሮቭ ከተያዘ አራት ቀናት በኋላ የአክራሪ እና ህገወጥ ይዘቶችን ለመቀነስ ጥረት ባለማድረግ እና በሌሎች ጭብጦች ክስ ቀርቦበታል።ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ባለቤት እና የኤክስ ባለቤት ኢሎን መስክ “ዱሮቭን ልቀቁት” የሚል ዘመቻ በመክፈት ለዱሮቭ አጋርነቱን አሳይቷል። ዱሮቭ በቁጥጥር ስር የዋለው በግል ጄቱ ከፓሪስ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቦርጌት አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰበት ወቅት ነበር።ዱሮቭ በ5.5 ሚሊዮን ዶላር በዋስ ወጥቶ በሳምንት ሁለት ጊዜ ለፖሊሲ ሪፖርት እንዲያደርግ ታዟል።
Al-Ain
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።