January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ኮሙኒኬሽንና ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጋር ከጥቂት ወራት በፊት የተጀመረውን ውይይት ዛሬ ቀጥለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤይጂንግ ቆይታቸው ከቻይና ኮሙኒኬሽን እና ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) ጋር ከጥቂት ወራት በፊት የተጀመረውን ውይይት ዛሬ ቀጥለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሲሲሲሲ የኢትዮጵያን ከተሞች በማዘመን የተጫወተውን ሚና ማድነቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ ከቻይና ጭምር የሌላ ሀገራት ቱሪስቶችን በሰፊው የመሳብ ትልም እውን ለማድረግ ሆቴሎችን፣ አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን መገንባት ቁልፍ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል።

EBC