ከቡርጀ ከሊፋ በቅርብ ርቀት እየተገነባ የሚገኘው “ቡርጀ አዚዚ” 725 ሜትር ቁመት ይኖረዋል ተብሏል ተከትሎ ሁለተኛው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ እንደሚሆን በትናንትናው እለት ነው የተገለጸው።በ2024 ጥር ወር ቁፋሮው የተጀመረው “ቡርጅ አዚዚ” ከኤምሬትስ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን እና ከሌሎች ተቋማት የሚሰጠው የግንባታ ፈቃድ ሲጠበቅ ቆይቷል።በዚህም ምን ያህል ፎቆች ያሉት ህንጻ እንደሚገነባ ሳይነገር ቆይቷል ።የአዚዚ ዴቨሎፕመንትስ መስራች ሚርዋይስ አዚዚ በትናንትናው እለት ግን ሲጠበቅ የነበረውን መረጃ አጋርተዋል። “ያቀረብነው ሁለት ዲዛይኖችን ነው ባለ526 እና 725 ሜትር ቁመት ህንጻ፤ ባለ725 ሜትሩ ህንጻ ዲዛይን ጸድቆልናል” ሲሉ ለዘናሽናል ኒውስ ተናግረዋል።ለሁለተኛውና ረጅሙ ህንጻ ዲዛይን ተጨማሪ የመሰረትና ቋሚ ግንባታዎችን ለማካሄድ አስቀድመን ተዘጋጅተናልም ነው ያሉት።
AL-AIN
More Stories
ሩሲያ በዩክሬን የኢነርጂ መሰረተ ልማት ተቋማት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለማቆም ተስማማች
አሜሪካ በየመን የሀውቲ ታጣቂዎች ላይ አዲስ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ
ትራምፕ “የወንበዴ” ቡድን አባላት ናቸው ያሏቸውን ከ200 በላይ ቬንዙዌላውያን ከአሜሪካ አባረሩ