በሥነጥበብ፣ በታሪክ እና በቅርስ ጠባቂነት፣ በንግግር አዋቂነት፣ በድርሰት ሥራዎቻቸው፣ በላቀ የምህድስን በሙያቸው እንዲሁም በበጎ አድራጊነት ሥራቸው ይታወቃሉ፡፡ ታታሪነትና እና ሀገርን መውደድ በተግባር ያሳዩን ሁለገብ ባለሙያ፣ ሁሉም በየዘርፉ እና በየአቅሙ ለሀገሩ ምን ማበርከት እንዳለበት ሠርተው ያሳዩ ሊቅ ናቸው፡፡ መኖሪያ ቤታቸው የኢትዮጵያ ባለውለታ የሆኑ ታላላቅ ሰዎችን በሚዘክሩ ታሪካዊ እና ዕድሜ ጠገብ ሥዕላት፣ ምስሎች እና ፎቶግራፎች፣ ቅርጻ ቅርጾች እንዲሁም የኢትዮጵያን ታሪክ እና ቅርስ በተመለከተ በጽሑፎች፣ በሰነድ፣ በምስል፣ በድምፅ እና በቪዲዮ ያሰባሰቧቸው መረጃዎችና ቅርሶች የተሞላ እንደሆነ የቅርብ ወዳጆቻቸው ይመሰክራሉ። ለኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ ያላቸው ክብር እና ተቆርቋሪነት እንዲሁም ለሕዝባቸው ያላቸው ፍቅር እናወገናዊነት በጣም ጥልቅ ነው ይባልላቸዋል።
EBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ