የአልናስሩ አጥቂ ሮናልዶ ማንችስተር ከገባበት ቀውስ ሊያወጣው እንደሚችልም ተገልጿልክርስቲያኖ ሮናልዶ ጥሩ የእግር ኳስ ቴክኒክ ዳይሬክተር እንደሚወጣው ማይክል ኦውን ተናገረ፡፡ፖርቹጋላዊው የቀድሞ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከሰሞኑ ወደ አሰልጣኝነት የመምጣት ፍላጎት እንደሌለው መናገሩ ይታወሳል፡፡ይህን ተከትሎም የቀድሞው የሊቨርፑል፣ ሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ የነበረው እንግሊዛዊው ማይክል ኦውን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡እንደ ማይክል ኦውን አስተያየት ከሆነ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጥሩ የእግር ኳስ ቴክኒክ ዳይሬክተር እንደሚወጣው ተናግሯል፡፡ሮናልዶ ጫማ ስለሚሰቅልበት ጊዜ ምን አለ?ሮናልዶ በ2016 በተካሄደው የአውሮፓ ዋንጫ ለይ በጉዳት ከወጣ በኋላ የብሄራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች ያበረታታበት እና የመራበት ሁኔታ ጥሩ የቴክኒክ ዳይሬክተር እና አሰልጣን እንደሚወጣው የሚሳይ ነውም ብሏል ኦውን፡፡ክርስቲያኖ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ባለፈ በውጤት ቀውስ ውስጥ ላለው ማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ አማራጭ ሊሆን እንደሚችልም ማይክል ኦውን ተናግሯል፡፡የክለቡ አሰልጣኝ የሆኑት ሆላንዳዊው ኤሪክ ቴን ሀግ መሰናበታቸው እንደማይቀር የተናገረው ማይክል ኦውን ለዚህ ደግሞ ክለቡ የቀድሞ ተጫዋቹ ክርስቲያኖ ሮናልዶን እንዲያይ መክሯል፡፡በሳውዲው አል ናስር ግብ እያስቆጠረ ያለው የ39 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቅርቡ በከፈተው የዩቲዩብ ቻናል ብዙ እይታ ካገኙ ሰዎች መካከል አንዱ ሆኗል፡፡
Al-Ain
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች