November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከመስከረም 1 ጀምሮ ይተገበራል – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በበጀት ዓመቱ ተቋሙ 42.5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አገልግሎቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲሱን የታሪፍ ማሻሻያ ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቋል።የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጃነር ሽፈራው ተሊላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከ50 ኪሎ ዋት እስከ 200 ኪሎ ዋት ድረስ የሚጠቀሙ ደንበኞች ድጎማ እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡ተግባራዊ የሚደረገው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ የመኖሪያ ቤት ፣ የንግድ ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራትን ታሪፍ ያካተተ ነው፡፡

Al-Ain