January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ሥራዎች ሀገሪቱ ራሷን ችላ ለምትቆምበት መፃዒ ተስፋ በር የሚከፍት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ሥራዎች ሀገሪቱ ራሷን ችላ ለምትቆምበት መፃዒ ተስፋ በር የሚከፍት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ “የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ሥራዎች እና የምግብ ሉዓላዊነት መንገድ በጠንካራ ትብብሮች ተሻግሮ ሀገራችን በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ሳትበገር ራሷን ችላ ለምትቆምበት መፃዒ ተስፋ በር የሚከፍት ነው” ብለዋል፡፡ በዘላቂ የግብርና ሥራ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ሥራ፤ ኢትዮጵያ ምርታማነትን ማላቅ፣ የአዝርዕት አይነትን ማብዛት ብሎም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ማሻሻል እንደምትችልም ገልጸዋል፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ትብብሮች የማኅበረሰብን አቅም ከፍ እንደሚያደርጉ፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ እና ፈጠራን እንደመያበረታቱም ጠቁመዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን በዘላቂ የምግብ ሥርዓት መሪ እንደሚያደርጋት እና የበለፀገ የምግብ ዋስትና የተረጋገጠበት መፃዒ ጊዜን ለህዝቡ እንደሚያረጋግጥም አመላክተዋል፡፡

EBC