January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጣሊያን እና ኬንያ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር አጉስቲኑ ፓሌሲ እና ከኬንያ አምባሳደር ጂዮርጂዮ ሞራራ ጋር ተወያይተዋል፡፡አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት አጉስቲኑ ፓሌሲ ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።በተጨማሪም የኢትዮጵያን የንግድ ልውውጥ እና ኢንቨስትመንት ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የኬንያ አምባሳደር ከሆኑት ጂዮርጂዮ ሞራራ ኦሪና ጋር በኢትዮጵያ እና ኬንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡

በዚህም ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስራቸውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩና የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

FBC