January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በእስራኤል ትናንት ግማሽ ሚሊየን ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ተነገረ

ሰልፈኞቹ የኔታንያሁ አስተዳደር ቀሪዎቹን 101 ታጋቾች እንዲያስለቅቅ ጠይቀዋልበጋዛ ስድስት ታጋቾች መገደላቸውን ተከትሎ እስራኤላውያን ቁጣቸውን በአደባባይ እያሰሙ ነው።የኔታንያሁ አስተዳደር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሶ ታጋቾችን ማስለቀቅ አልቻለም ያሉ 500 ሺህ የሚገመቱ ሰልፈኞች በቴል አቪቭ፣ እየሩሳሌምና ሌሎች ከተሞች ድምጻቸውን አሰምተዋል።ሰልፈኞቹ በእየሩሳሌም መንገድ ዘግተው በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ዙሪያ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።የቴል አቪቭ ጎዳናዎችም የሟቾቹን ታጋቾች ምስሎች በያዙ ሰልፈኞች ተሞልተው መዋላቸውን ነው ሬውተርስ ያስነበበው።ሰልፈኞቹ የኔታንያሁ አስተዳደር ቀሪዎቹን 101 ታጋቾች ለማስለቀቅ በፍጥነት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርስ ጠይቀዋል።

Al-Ain