January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሀገር አቀፍ የሰላምና ፀጥታ ምክክር መድረክ መካሄድ ጀመረ

የሰላም ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ፀጥታ ምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል።በሰላም ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት ሀገር አቀፍ የሰላም ግንባታና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ላይ በመድረኩ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል።በፌዴራሊዝም፣ በመንግስታት ግንኙነትና በግጭት አስተዳደር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግበትም ተጠቁሟል።

EBC