ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ10 ሚሊዮን ብር እንደተቋም እንዲሁም ከደንበኞች ያሰባሰበውን 1.35 ሚሊዮን ብር በድምሩ ከ11.35 ሚሊዮን ብር በላይ አስረከበ፡፡ኩባንያው በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋው የተጎዱትን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት ለማገዝ የሚያስችለውን የብር ድጋፍ ከደንበኞች፣ በቴሌብር እና በ8090 አጭር ቁጥር ያሰባሰበውን ድጋፍ ጨምሮ ለጎፋ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ምላሽ ፈንድ በዛሬ ዕለት አስረክቧል፡፡የኩባንያው ከፍተኛ አመራር ተወካዮች በጎፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ተገኝተው በዜጎች ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የገለጹ ሲሆን በዚህም ወቅት ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እያደረገ የሚገኘውን ሁለገብ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፣ ዜጎችን የማቋቋሙ ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ማህበረሰቡ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተከፈቱ የቴሌብር እና የአጭር ቁጥር 8091 በመጠቀም አቅም የፈቀደውን ድጋፍ ማድረጉን
EBC
More Stories
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ የአዳር ትምህርት ተመቻችቶ የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩ የበለጠ ውጤት እንድናስመዘግብ አግዞናል ሲሉ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ የአዳር ትምህርት እድል ያገኙ ተማሪዎች ገለፁ ።