የዓየር ንብረት ለውጥን ለመግታት በችግኝ ተከላ ከመትጋት ባሻገር የደን ሐብትን መንከባከብ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ዓለም ላይ ከፍተኛ የብዝሃ ህይወት ክምችት ካለባቸው ስፍራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የካፋ ጥብቅ ደን፤ የተወዳጁ የካፋ የጫካ ቡና መገኛም ነው። በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ከተመዘገቡ የሀገራችን ድንቅ ተፈጥሯዊ ስፍራዎች ውስጥ አንዱ መሆኑም ይታመናል፡፡ የካፋ ጥብቅ ደን በደቡባዊ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 460 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚገኝ የብዝሃ ህይወት ክምችት መገኛ ቦታ ነው፡፡ 540 ሺህ ሄክታር መሬት የሚያካልለው የካፋ ጥብቅ ደን 5 ሺህ የሚጠጉ የዕፅዋት ዝርያዎችን በውስጡ ይዟል፡፡ 17 አይነት ብርቅዬ ሀገር በቀል የዕፅዋት ዝርያዎችም በዚሁ የጥብቅ ደን ማዕከል ውስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ። በዚህ ምድረ ገነት ጫካ ውስጥ “ጎጀብ”፣ “ዲንጫ” እና “ወሺ” የተሰኙ ሦስት ትልልቅ ወንዞች ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ ይፈሳሉ። ደን ለካፋ ህዝብ ሁሉ ነገሩ ነው፤ መኖሪያው፣ ህክምናው እና ምግቡም ጭምር እንደሆነ ነዋሪዎቹን ጨምሮ ወደ ቦታው ያቀና ሁሉ ምስክር ነው። ይህ ጥብቅ ደን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም ምርጥ የተፈጥሮ ስጦታ በመሆኑ ዩኔስኮ ዕውቅና ሰጥቶት መዝግቦታል፡፡
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።