የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባንግላዲሽ ዋና ከተማ ወደሆነችው ዳካ አዲስ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ ወደ ዳካ ከተማ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ስድስት ቀናት አዲስ በረራ እንደሚጀምር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡የበረራ መስመሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ እስያ ያለውን ተደራሽነት የሚያሰፋ ሲሆን በባንግላዴሽ እና አፍሪካ መካከል ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
FBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ