የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በዌስትባንክ በርካታ ግጭቶች ተከስተዋል እስራኤል በዌስትባንክ ባካሄደችው ዘመቻ የሀማስን መሪ ገደልኩ አለችየጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በዌስትባንክ በርካታ ግጭቶች ተከስተዋል የእስራኤል ጦር፣ እስራኤል ዘወርራ በያዘቻት ዌስትባንክ የሀማስን መሪ እና ሌሎች ወታደሮችን ጄኒን ውስጥ መግደሉን አስታውቋልእስራኤል በዌስትባንክ ባካሄደችው ዘመቻ የሀማስን መሪ ገደልኩ አለች።የእስራኤል ጦር፣ እስራኤል ዘወርራ በያዘቻት ሰሜናዊ ዌስትባንክ እያደረገ ባለው መጠነሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ የሀማስን መሪ እና ሌሎች ወታደሮችን ጄኒን ውስጥ መግደሉን አስታውቋል።ጦሩ ባወጣው መግለጫ የእስራኤል ኃይሎች ዊሳም ሀዜምን በመኪና ውስጥ መግደላቸውን እና “ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ በነበሩ ሁለት ሽብርተኞች” ላይ የአየር ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጿል።የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር በደቡብ ምስራቅ ጄኒን በምትገኘው የዛባዳህ ከተማ አቅራቢያ ሶሰት ወንዶች ተገድለዋል ብሏል። ቢቢሲ የፍልስጤም መገናኛ ብዙኻንን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስራኤል ኃይሎች በህንጻዎች እና በከተማዋ መጠለያ ካምፖች የሚገኙ መሰረተልማቶችን ካወደሙ በኋላ ከቱልክአርም ወጥተዋል።ባለፈው ሀሙስ በቱልክአርም ውስጥ መሪያቸውን ጨምሮ አምስት የታጣቂውን ቡድን አባላት መግደሉን የገለጸው የእስራኤል ጦር ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጠም። የእስራኤል ጦር “ሽብር ካከሸፈ፣ የሽብርተኞችን መሰረተልማቶች ካወደመ እና ታጣቂዎች ካጠፋ” በኋላ በቱባስ አቅራቢያ ከሚገኘው የአል ፋራ መጠለያ ካምፕ መውጣቱን አስታውቋል።እስራኤል በአስርት አመታት ውስጥ በዌስባንክ ካካሄደቻቸው ትላልቅ ዘመቻዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በዚህ ዘመቻ ቢያንስ 19 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዜ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።እንግሊዝ ባለፈው አርብ እለት “እስራኤል እየተጠቀመችው ያለው የዘመቻ ስልት እና እየወጡ ያሉ የንጹሀን ግድያ እና የመሰረተልማቶች ውድመት ሪፖርቶች” እንዳስጨነቋት ገልጻለች።”ከባድ የአለመረጋጋት ችግር ሊከሰት ስለሚችል፣ ውጥረቱን በአስቸኳይ ማርገብ ያስፈልጋል” ብለዋል የሀገሪቱ የውጭ ቢሮ ቃል አቀባይ።የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም የእስራኤል ወረራ ያለውን አደገኛ ሁኔታ የሚባብስ ነው ሲሉ በትናንትናው እለት አስጠንቅቀዋል።ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ድንበር ጥሶ ያልተጠበቀ ጥቃት ከሰነዘረ ወዲህ በዌስትባንክ በርካታ ግጭቶች ተከስተዋል።የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት በድርድር መቋጨት ባለመቻሉ ምክንያት ጦርነቱ 10 ወራትን አስቆጥሯል።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም