የባህላዊ ትውፊትና የጥበብ ማህደር በሆነችው አክሱም የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን፣ ባህላዊና ሕዝባዊ በዓላት ትውፊታቸውን ሳይቀይሩ በማልማት ወደ ሕዝባዊ ጥቅም እንቀይርቸዋለን ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ። በአክሱም ከተማና አካባቢው የዓይኒዋሪ የልጃገረዶች በዓል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ከአክሱም ከተማና ከማዕከላዊ ዞን ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የዓይኒዋሪ ልጃገረዶች የተለያዩ አልባሳት ለብሰውና በጌጣጌጥ ደምቀው በዓሉን እያከበሩ ናቸው። ዛሬ በተጀመረው በዚሁ በዓል ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለጹት፤ የአክሱም ልጃገረዶች ዓይኒዋሪን በዓል ከዘመን ዘመን በቅብብሎሽ ሲያከብሩትና ሲያደምቁት ቆይተዋል። አክሱም የባህላዊ ትውፊትና የጥበብ ማህደር መሆኗን ጠቁመው፤ ለቀጣይም የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ልንሰራ ይገባናል ብለዋል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።