November 23, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በስልጤ ዞን በጎርፍ አደጋው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 7ሺህ ደርሷል፡- የዞኑ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ጽ/ቤት

በስልጤ ዞን ሰሞኑን በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተፈናቃይ ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የዞኑ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡ የፅ/ቤቱ ኃላፊ ወሲላ አሰፋ ለኢቢሲ ሳይበር እንደገለፁት፤ በጎርፉ አደጋው 7ሺ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ 1300 ሄክታር መሬት ማሳ ከጥቅም ውጭ ሆኗል፤ 6 ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 1ሺ ቤቶች በጎርፍ ተውጠዋል፡፡ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ እየተፈናቀሉ ያሉ ሰዎች ቁጥር አሁንም እየጨመረ መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ በሁለቱ ወረዳዎች በጎርፍ ተውጠው የነበሩ ቀበሌዎች ከ6 ወደ 8 ማደጋቸውንና በውሃ የተዋጡ ትምህርት ቤቶች ቁጥር 6 መድረሱን ተናግረዋል፡፡

You may have missed