January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፈረንሳይ በቴሌግራም መስራች ፓቨል ዱሮቭ ላይ ክስ መሰረተች

ቅዳሜ እለት በፈረንሳይ በፖሊስ ቁጥጥር ሰር ውሎ የነበረው ፓቨል ፈረንሳይን ለቆ እንዳይወጣ እግድ ተጥሎበታልፈረንሳይ በቴሌግራም ማህበራዊ ትስስር ገጽ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቭል ዱሮቭ ላይ ክስ መሰርታለች፡፡ከ900 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ቴሌግራም የተደራጁ ወንጀሎችን ለማከናውን ውሏል በሚል ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ባሰለፍነው ቅዳሜ ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኝ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር የዋለው ፓቨል በአምስት ሚሊየን ዮሮ ዋስትና ከተለቀቀ በኋላ ፈረንሳይን ለቆ እንዳይወጣ እግድ ተጥሎበታል፡፡

Al-Ain