January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2016 በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 43 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንዳሉት÷ የተቀላጠፈና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 427 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡በ2016 በጀት ዓመት በከተለያዩ የገቢ ምንጮች 42 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘት መቻሉንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግርን ለመቅረፍም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችን አቅም የማሳደግ፣ የመፈተሽና የመጠገን ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡