ትላንት ምሽት የተጀመረው የሀገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውይይት እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናልበአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን የተመራ ልዑክ ከቻይና ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር እየመከረ ነው።በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን የተመራ ልኡክ በትላንትናው እለት ወደ ቤጂንግ አቅንቷል፡፡በጆ ባይደን የአስተዳደር ዘመን የተካረረ ውጥረት ውስጥ የሚገኙት ቤጂንግ እና ዋሽንግተን ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብ እየመከሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡የቀድሞ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በ2022 መጨረሻ ወደ ታይዋን ማቅናታቸው የባይደን እና የሺ ዢንፒንግን አስተዳደርን ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከቷቸው እንደነበር ይታወሳል፡ከዚህ ባለፈም በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ቻይና ለሞስኮ እያደረገች ነው በሚባለው ድጋፍ ከምእራባውያን ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ውይይት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው ሱሊቫን ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ይ ጋር በቀጠናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይታቸው አተኩሯል፡፡ለሶስት ቀናት በሚቆየው የሀገራቱ ምክክር ንግድ፣ መካከለኛው ምስራቅ ፣ የዩክሬን ጦርነት ፣ ታይዋን እና የደቡብ ቻይና ባህር አጀንዳ ላይ ልኡካኑ እንደሚነጋገሩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡በትላንትናው እለት በሰሜናዊ ቤጂንግ አቅራቢያ በሚገኝ ሪዞርት ለአሜሪካ ልኡካን በተደረገ የእራት ግብዣ ውይይታቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ በዛሬው እለት ደግሞ በቀጠናዊ እና በጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ልነታቸውን ለማጥበብ ይነጋገራሉ ነው የተባለው፡፡ጄክ ሱሊቫን ሁለቱ ሀገራት በንግድ እና በፖለቲካ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ በልዩነቶቻቸው ዙርያ ደግሞ ለመቀራረብ አሜሪካ ዝግጁ ናት ነው ያሉት፡፡ሮይተርስ እንደዘገበው ጥቂት ወራት በቀረው የባይደን አስተዳደር ከቻይና ጋር የሚገኙበትን ውጥረት ማቀዝቀዝ መፈለጋቸው ለካማላ ሃሪስ የውድድር ጊዜ ሁኔታዎችን ቀለል ለማድረግ በማስብ ነው ብሏል፡፡ሱሊቫኒ በዚህኛው ጉብኝታቸውም በሁሉም ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ እንደማይደርሱ ቢጠበቅም ሀገራቱ በጦር አመራሮቻቸው በኩል ንግግር እንዲጀመር ለማስቻል እና በታይዋን ጉዳይ ያሉ ውዝግቦችን ለማርገብ ትኩረት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ቤጂንግ በበኩሏ ወደ አሜሪካ በሚላኩ ምርቶቻ ላይ ከሚጣሉ ታሪፎች ጋር በተያያዘ እና የታይዋን ባለቤትነት ላይ አቋሟን እንደምታንጸባርቅ ይጠበቃል፡፡ ትላንት ምሽት የተጀመረው የሀገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውይይት እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
Al-Ain
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።