October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በማሻ ወረዳ በግንባታ ህደት ላይ የሚገኘው የቄጃ ጤና ጣቢያ ባለመጠናቀቁ አገልግሎት ለመስጠት እንቅፋት ሆኗል ተባለለ

ችግሩ መፍትሔ ለማበጀት ከሸካ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ጋር እየተሰራ መሆኑንም ወረዳው አሳውቋል። በሸካ ዞን ማሻ የምርጫ ጣቢያ ተመራጭ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራ አንደሞና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ጉብኝት ተደርጓል። የሬድዮ ጣቢያችን የሸካ ዞን ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ካዳኔ ከሲቶ በስልክ በስልክ በሰጡት መረጃ አራት ብሎክ ያለው የጤና ጣቢያዉ በ2008 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረ ሲሆን ስራው ያስጀመረው ኮንትራክተር ስራ በማቋረጡ ምክንያት ተጓቶ መቆየቱን አንስተው አሁን ላይ ከአድስ ኮንትራክተር ጋር በመሆን የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ግንባታው ወደ መጠናቀቁ ደረጃ መድረሱን ገልጸዋል።

ዘጋቢ ሀና ግርማ