ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በዓለም አቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳልኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ስርአት መከተል ከጀመረች በኋላ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በአለምአቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።በዚህም ባንኩ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በድረ ገጹ ይፋ እያደረገ ይገኛል።ብሄራዊ ባንክ የዛሬ የነሃሴ 20 2016 የወርቅ መግዣ ዋጋን ይፋ ሲያደርግ ባለ 24 ካራት 1 ግራም ወርቅ 80.5852 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 9 ሺህ 218 ብር እየገዛ መሆኑ ተመላክቷል።ባለ 23 ካራት 1 ግራም ወርቅ 77.2275 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 833 ብር እየገዛ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።ባለ 22 ካራት 1 ግራም ወርቅ ደግሞ በ73.8698 ዶላር (8 ሺህ 449 ብር) እየገዛ ይገኛል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በቀጣዩ ሰንጠረዥ ይመልከቱ፦
Woreda to World
More Stories
ከውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር እየተዘጋጁ መሆኑን ባንኮች ገለጹ
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ
ለ5 ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የሥራ ፈቃድ ተሰጠ