እስራኤል ከሐማስ እና ሂዝቦላህ ጋር ጦርነት መጀመሯን ተከትሎ አለኝ የምትላቸውን ባለ ስልጣናት ወደ ዚህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አስገብታለችበእስራኤል የተሰራው የክፉ ቀን መሸሸጊያከ11 ወራት በፊት ሐማስ ያልታሰበ ጥቃት በእስራኤል ላይ መጣሉን ተከትሎ ነበር በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነገሰው፡፡ለትንሽ ቀናት ከቆየ በኋላ ወደ ስምምነት ይመጣሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ይህ ጦርነት መልኩን እየቀያየረ አንድ ዓመት ሊሆነው አንድ ወር ብቻ ቀሮታል፡፡ይህን ተከትሎ እስራኤል ለክፉ ቀን መሸሸጊያ በሚል ከመሬት በታች የሰራችው መሸሸጊያ ባለስልጣናትን ከጥቃት መጠበቂያ አድርጋዋለች፡፡የእስራኤል ወታደራዊ እና ሲቪል መሪዎች በሐማስ፣ ሂዝቦላህ ወይም ኢራን ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ወደ ክፉ ቀን መሸሸጊያው እንዲገቡ ማድረጓ ተገልጿል፡፡ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ የተለያዩ ወሳኝ ስብሰባዎችን እና ወታደራዊ ትዕዛዝ ማስተላለፍ የሚያስችል መሰረተ ልማት የተገጠመለት ሲሆን ከየትኛውም ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች መከላከያዎች አሉትም ተብሏል፡፡በእስራኤል በኤርትራውያን ስደተኞች መካከል በተከሰተ ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉበመሀል እየሩሳሌም ተራራዎች ላይ መሰራቱ የተገለጸው ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ጥቅም ላይ ውሎ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ አገልግሎት እንደገባ ተገልጿል፡፡ሻባክ የሚል ስያሜ ያለው ይህ የክፉ ቀን መሸሸጊያ 95 በመቶ አካሉ በመሬት ውስጥ ሲገኝ ባንድ ጊዜ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከየትኛውም አደጋ ጠብቆ ያስጠልላል፡፡እስራኤል ከሊባኖስ ጋር ጦርነት በገባችበት ከ18 ዓመት በፊት ይህንን የክፉ ቀን መሸሸጊያ እንደገነባችው እና መጠቀም እንደጀመረች ይታመናል፡፡ሀገሪቱ የክፉ ቀን መሸሸጊያውን ለመስራት ቢሊዮን ዶላሮችን ወጪ እንዳደረገችበት ሲገለጽ የግንባታ ዲዛይኑ በአሜሪካ ዋሸንግተን ካለው ጋር ተመሳሳይነት እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
Al-Ain
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት ገለጸች