October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፍ የተመዘገበውን ውጤት በ2017 ለመድገም የሁሉም ህብረተሰብ ርብርብ ይጠይቃል ፦

አቶ አልማው ዘውዴየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሠረት በመማር ማስተማሩ ዘርፍ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በክልሉ በ2016 የትምህርት ዘመን ከተመዘገበው ውጤት የበለጠ ለማስመዝገብ በተቀናጅ መንገድ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።እንደ ሀገር ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ሐሳብ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ያስጀመሩት ለመማር ማስተማር ሚቹ ያልሆኑና ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን መለየትና ደረጃቸውን ማሳደግ ከተሰሩት ሪፎርሞች መካከል ይገኙበታል ብለዋል።