January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሩሲያ እና ዩክሬን 115 የጦር እስረኞችን ተለዋወጡ

አረብ ኤምሬትስ ሁለቱ ሀገራት ምርኮኞችን እንዲለዋወጡ የማደራደሩን ሚና ተወጥታለች

ኤምሬትስ ሩሲያና ዩክሬን የእስረኞች ልውውጥ ስምምነት እንዲደርሱ ስታደርግ የዛሬው ለሰባተኛ ጊዜ ነው ተብሏልሩሲያ እና ዩክሬን በዛሬው እለት የጦር ምርኮኞችን ተለዋውጠዋል።በአረብ ኤምሬትስ አደራዳሪነት ከስምምነት በተደረሰው የእስረኞች ልውውጥ ሁለቱ ሀገራት እኩል 115 እስረኞችን ተለዋውጠዋል ብሏል አናዶሉ በዘገባው።ዩክሬን ከ18 ቀናት በፊት በምዕራባዊ ሩሲያ ኩርስክ ክልል ጥቃት ከከፈተች በኋላ ከሞስኮ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የእስረኞች ልውውጥ ያደረገችው።ሩሲያ የለቀቀቻቸው የዩክሬን ወታደሮች የሀገራቸውን ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ ታይተዋል።

Al-Ain