ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ለታሪካዊው የችግኝ ተከላ በዛሬዋ ታሪካዊት ቀን በተፈጥሮ ስጦታ፣ በማዕድን ሃብትና ለም ምድር በሚታወቀው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተገኝተናል ብለዋል።በዛሬው ሁነት መጨረሻ በመላው ሀገራችን ባለፉት አምስት ዓመታት የተተከልናቸው ችግኞች ወደ 40 ቢሊየን ይደርሳሉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡ባለፈው ዓመት ከተተከሉት ችግኞች 50 ከመቶው በምግብ ዋስትና፣ አፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆት ላይ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ የተተከሉ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡በቀጣይም እንደ አባይ ተፋሰስ ባሉ አካባቢዋች ችግኞችን በመትከል የውሃ ጥበቃ ሥራን ልንደግፍ ይገባል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡፡
FBC
More Stories
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በሩሲያ የድል በዓል የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ ተሳተፉ
አሜሪካዊው ሮበርት ፕሪቮስት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመረጡ