ክብሩን፣ ድሉን፣ ውጤቱን፣ ምስጋናውን ፈጣሪ ይውሰድና፤ ማልደን የተነሳንበት ኢትዮጵያን በ600 ሚሊዮን ችግኞች አረንጓዴ የማልበስ ሕልም 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የታለመለትን ፍሬ በማፍራቱ እጅግ ደስ ብሎኛል ብለዋል አቶ አደም ፋራህ።ህፃናት፣ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ወጣቶች ስለ ነገዋ ኢትዮጵያችን ብለው፣ ትውልድን አስበው አፈር እየማሱ ደፋ ቀና ሲሉ ማየት ልብን በሃሴት ይሞላል ነው ያሉት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ።በዘር፣ በፆታ፣ በእድሜ፣ በሙያ ሳንከፋፈል ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ትውልዷ ብለን ዛሬ ላይ የሰራነው ገድል ነገ በታሪክ ዘንድ ወርቃማ ካባ እንደሚያጎናፅፈን ፈፅሞ ጥርጥር የለውም ብለዋል አቶ አደም ፋራህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የደስታ መግለጫ መልዕክት።ዛሬ የተከልነውንም ተንከባክበን በማፅደቅ፣ የአረንጓዴ አሻራ ትጋታችንን በእጥፍ በመጨመር የኢትዮጵያ ብልፅግና እና ስልጣኔ በዛፎች እና በተፈጥሯዊ በረከቶች መሀል እንዲዋቀር የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣታችንን እንቀጥላለን፤ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።