ኒውራሊንክ ኩባንያ በነርቭ ጉዳት ምክንያት የመንቀሳቀስ ችግር ላጋጠማቸው ሰዎች ተስፋን ይዞ ቺፑ የተገጠመለት ሰውም ነርቮቹ መንቀሳቀስ ጀምረዋል ተብሏል
መጥቷልየኢለን መስኩ ኒውራ ሊንክ ሁለተኛውን ቺፕ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ ገጠመ፡፡የአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢለን መስክ ንብረት የሆነው የባዮ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኒውራሊንክ ባለፈው ጥር ወር የመጀመሪያውን ችፕስ በሰው አእምሮ ውስጥ መቅበሩ ይታወሳል፡፡የመስክ ባዮቴክ ኩባንያ የ30 አመት እድሜ ባለው ግለሰብ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ችፕስ የገጠመው ባለፈው ጥር ወር ነበር።ኩባንያው አሁን ደግሞ ሁለተኛውን ሙኩራ አሌክስ በሚል ስም ለሚጠራ አካል ጉዳተኛ አዕምሮ ውስጥ መግጠሙን እና ግለሰቡም ለውጥ ማሳየት ጀምሯል ብሏል።የሳንቲም መጠን ያላትን ቺፕስ የሰው ልጅን እንቅስቃሴ ፍላጎት ከሚያዘው የአእምሮ ክፍል ላይ በቀዶ ጥገና እንድትቀመጥ የሚደረግ ነው።ይህቺ ቺፕስ የአእምሮን እንቅስቃሴ በመመዝገብ እና የእንቅስቃሴ ፍላጎትን ወደሚተረጉም ማቀላጠፊያ መተግበሪያ ወይም አፕ ለማስተላለፍ ጥቅም ላይ ትውላለች።
AL-AIN
More Stories
የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቲክ ቶክ እንዲሸጥ የሚያስገድድ ውሳኔ አሳለፈ
ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ያደርጋል
የቴሌግራም ኃላፊ ዱሮቭ በፈረንሳይ የቀረበበት ክስ “ድንገተኛ” እና “የተሳሳተ” ነው አለ