November 21, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን የተመራ ልዑካን ቡድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አስመልክቶ ለቡድኑ ገለጻ አድርገዋል። በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የትብብር ስራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰራም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን የጉብኝቱ ዓላማ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት ልምድ መመልከትና ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ፤ በተለይም ደግሞ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስራ መስራቷን ከጉብኝቱ መረዳታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነቷን እና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት ሩሲያ ያላትን ልምድ ከማካፈል ጀምሮ በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አምባሳደሩ መናገራቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት

EBC

You may have missed