October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በመጪው በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡- የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

በአቅርቦት እጥረት ምክንያት ለመጪው በዓል በሚውሉ ምርቶች ላይ የዋጋ መናር እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ከ115 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ጅቡቲ መድረሱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በቀናት ውስጥ ወደ ምርት ማዕከል እንደሚገቡም ነው የጠቆሙት፡፡አክለውም ሌሎች መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች ወደ ምርት ማዕከል እንደሚገቡም ጠቅሰዋል፡፡ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል እንዳይጎዳ መንግስት በጥንቃቄ እየሰራ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ስራው ውጤታማነት እያሳየ መሆኑን ገልጸው፣በምርት በእጥረት ምክንያት የሚፈጠር የዋጋ ንረት እንደማይኖር ነው የተናገሩት፡፡

EBC