የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ጎብኝዎችን መሳብ እንዲችል፣ ገጽታ መገንቢያ እና ሃብት መፍጠሪያ እንዲሆን እንሠራለን ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡ርዕሰ መሥተዳድሩ ለሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡በመልዕክታቸውም÷ በክልላችን በዋግ ኽምራ፣ ሰሜን ወሎ እና ሌሎች አካባቢዎች ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የሚከበረው ሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በልጃገረዶች እና ወጣቶች በባሕላዊ ጭፈራ እና በሃይማኖታዊ ክዋኔዎች የሚከበር ዘመን ተሻጋሪ እና ብዙ ዓመታትን አብሮን የኖረ የሕዝብ በዓል ነው ብለዋል፡፡ከሃይማኖታዊ አከባበሩ በተጓዳኝም ባሕላዊ መስተጋብር የሚያብብበት እና አብሮነት የሚደምቅበት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡በዓሉን ስናከብርም ሕዝባችን ለዘመናት የገነባውን እሴት በማክበር እና በማሳደግ ከትውልድ ትውልድ በድምቀት እንዲሸጋገር በመሥራት ሊሆን ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡በቀጣይም የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችን መሳብ እንዲችል፣ ገጽታ መገንቢያ እና ሃብት መፍጠሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በጋራ እንሠራለን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።