የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የመረጃ ተቋማት በድንበር አካባቢ እና በኬኒያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድን አመራሮች እና ታጣቂዎች ላይ የጀመሩትን ኦፕሬሽን አጠናክረው ለመቀጠል አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በኬኒያ የመረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ኑረዲን መሐመድ ሀጂ የተመራ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ዳይሬክተር ጄነራሉ ከሉዕካን ቡድናቸው ጋር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
EBC
More Stories
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው