ወንጀለኛው በጥንቆላ ስራ የሚተዳደር ሲሆን ሴቶችን በማታለል ሲደፍር ነበር ተብሏልኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣች፡፡የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር የሆነችው ኢራን በአስገድዶ መድፈር ትፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ገድላለች፡፡የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት ከሆነ በማዕከላዊ ኢራን ካሉ ግዛቶች አንዱ በሆነው ዝድ ክልል አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ግለሰቡ በጥንቆላ ይተዳደራል የተባለ ሲሆን ለአገልግሎት የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ኢራን በሞስኮ ለእይታ ያቀረበችው ድሮን – “ሞሃጀር-10”በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ መደረጉን አል አረቢያ ዘግቧል፡፡ኢራን በአስገድዶ ደፈራ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡በኢራን የሞት ፍርድ ያስቀጣሉ ከተባሉ ወንጀሎች መካከል አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ሀገሪቱ በየዓመቱ በርካታ ዜጎችን በሞት የምትቀጣ ሲሆን ይህም በመላው ዓለም የሞት ቅጣት ከሚተላለፍባቸው ዜጎች መካከል አብዛኛው በኢራን ይፈጸማል፡፡
AL-AIN
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች